📌📌በሳይንስ የተረጋገጡ 10 የተልባ ፍሬ የጤና ጥቅሞች፤
✅1.የተልባ ፍሬ መጠቃሚ የምግብ ይዘቶች የተሞላ ነው፡፡
ከጥንታዊ ስልጣኔ ጀምሮ የተልባ ፍሬ ጠቃሚ ከሚባሉት ውስጥ ይመደባል፡፡ ቡናማ እና ወርቅማ አይነቶች አሉ፤ ሁለቱም ተመሳሳይ ጠቀሜታ አላቸው፡፡
አንድ የሻይ ማንኪያ የተልባ ፍሬ በውስጡ ተመጣጣኝ የሆነ የካሎሪ፣ ፕሮቲን፣ ካርቦሐይድሬት፣ ፊይበር፣ ቅባት፣ ኦሜጋ 3፣ ቪታሚን ቢ 1፣ ቢ 6፣ ፎሌት፣ ካልሺየም፣ አይረንእና ማንግኒዢየም ይዘት አለው፡፡
ለጤና የሚጠቅመው በተለይ በኦሜጋ 3 እና ፋይበር ይዘቱ ነው፡፡
✅2.የተልባ ፍሬ በኦሜጋ 3 የበለፀገ ነው፡፡
በተለይ የስጋ እና የወተት ተዋዕፆ ለማይወስዱ ሰዎች የተልባ ፍሬ ሁነኛ የኦሜጋ 3 ምንጭ ነው፡፡ መሰል የምግብ ይዘት ያላቸው የልብን ጤንነት ለመጠበቅ እና ጭንቅላት ውስጥ ደም እንዳይፈስ እንደሚረዱ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
✅3.የተልባ ፍሬ ካንሰርን ሊከላከል የሚችል ውህድ አለው፡፡
እነዚህ ውህዶች የአንታይኦክሲዳንት እና ኤስትሮጅን ባህሪ ስላላቸው በካንሰር (እንደ የጡት ካንሰር እና የፕሮስቴት ካንሰር) የመያዝ እድልን በመቀነስ ጤንነትን ይጠብቃሉ፡፡
✅4.የተልባ ፍሬ ከፍተኛ የፋይበር መጠን ይይዛል፡፡
ተልባን የእለት ተእለት ምግቦት ውስጥ ማስገባት የምግብ መፈጨትን ከማሳለጡ በላይ የምግብ መፈጨት ላይ የሚሳተፉ አትን ጤንት ያሻሽላል፡፡
✅5የተልባ ፍሬ የደም ውስጥ ኮሌስትሮል መጠን ይቀንሳል፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በቀን 3 የሻይ ማንጂያ ተልባ ለወራት መመገብ የመጥፎ ኮሌስትሮል መጠንን እጅጉን በመቀነስ ጥሩ የሚባለውን ኮሌስትሮል ይጨምራል፤ ይህም እድሜአቸው ከ45 በላይ የሆኑ ሴቶች ላይ ጎልቶ ታይቷል፡፡ ይህም የሚሆነው በተልባ ውስጥ ያለው ፋይበር ከሃሞት ጨው ጋር በሚጣበቅበት ጊዜ ከሰውነት ስለሚወገድ ነው፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ የልብን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል፡፡
✅6.የተልባ ፍሬ የደም ግፊትን ሊያስተካክል ይችላል፡፡
ተልባ የደምግፊትን እንደሚቀንስ ብዙ ጥናቶች አሳይተዋል፡፡ በቀን 3 የሻይ ማንኪያ ተልባ መመገብ ለዚህ ይረዳል፡፡ ተያይዞም የሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡
✅7.ከፍተኛ የፕሮቲን መጠን ይይዛል፡፡
ተልባ በጣም ጥሩ የሚባል የፕሮቲን ምንጭ ነው፡፡ በዚህም ምክንት የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም በመጨመር፣ ኮሌስትሮልን በመቀነ፣ ካንሰርን በመከላከል እና በፀረ-ፈንገስ ባህሪው ወደር አይገኝለትም፡፡ የስጋ ተዋፅዖ ለማይወስዱ ሰዎች ተመራጭ ነው፡፡
✅8.የተልባ ፍሬ የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ለማስተካከል ይረዳል፡፡
በአለምአቀፍ ደረጃ የስኳር በሽታ ዋነኛ የጤና ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡ የስኳር በሽተኞች መደበኛ አመጋገባቸው ላይ ከ1-2 የሻይ ማንኪያ ተልባ ቢያንስ ለአንድ ወር ቢጨምሩ በአስገራሚ ሁኔታ የስኳር መጠናቸው ይቀንሳል፡፡ ይህም የሆነው የተልባ ፍሬ በውስጡ ባለው የማይሟሟ የፋይበር መጠን ምክንያት ነው፡፡
✅9.የተልባ ፍሬ የሰውነትን ክብደት ለመቀነስ ሊረዳ ይችላል፡፡
በተለይ በየሰዓቱ ምግብ መብላት ለለመዱ ሰዎች ተልባን (ከ1-2 የሻይ ማንኪያ) በመጠጦ ላይ በየቀኑ መጨመር የረሐብ ስሜትን ያርቃል፡፡ ምክንያቱም በተላባ ውስ ያለው የሚሟሟ የፋይበር አይነት በጨጓራ የምግብ መፈጨትን ሲያዘገይ፤ የረሐብን ስሜት እና የምግብ ፍላጎትን ይቀንሳል፡፡
✅10.የተልባ ፍሬን የተለያዩ የምግቦች አይነቶች ውስጥ ሊጨመር ይችላል፡፡
የተልባ ፍሮ ከብዙ የምግብ አይነቶች ጋር ይሄዳል፡፡ ይህም በየቀኑ እንዲወሰድ ያስችለዋል፡፡
ለምሳሌ፤
-የመጠጥ ውሃ ውስጥ መጨመር
-ሰላጣ ሲሰራ የተልባ ዘይት መጠቀም
-ለቁርስ የሚመገቡት አጃ ወይም ገብስ ላይ የተፈጨ ተልባ መጨመር
-የሚወዱት የእርጎ አይነት ውሰስጥ መጠቀም
-የሚጋግሩት ኩኪስ፣ ኬክ እና ዳቦ ላይ መጨመር
– ከሙዝ ወይም የሚወዱት ፍራፍሬ ጋር አብሮ ፈጭቶ መጠጣት
-ከስጋ ጋር አብሮ መቀቀል ወይም መጥበስ
Reviews
There are no reviews yet.